
ትዕዛዝ 2023-03 – በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ፕሮግራም ማቋቋም
ትዕዛዝ 2023-03
የሲያትል ወደብ ኮሚቴ ትዕዛዝ
በሲያትል-ታኮማ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ እስከ አምስት አመት ለሚሆን ጊዜ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ
አገልግሎት ክፍያ ፕሮግራም ለማቋቋም።
የቀረበው
ፌብሩዋሪ 14፣ 2023
መግቢያ
የሶስት አመት ለሙከራ የተሰራ ፕሮጀክትን ተከትሎ፣ የሲያትል ወደብ ኮሚቴ ከታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ለሙከራ የተሰራ
ፕሮግራም አንቀሳቃሾች ጋር በጠንካራ ቁጥጥር እና በባለ ድርሻ አካላትን ማግኘት ላይ ተሰማርቷል። የሚከተለው ትዕዛዝ እንደ
ትምህርት እና የቨርቿል ወረፋ አማራጭ መዘርጋት የመሳሰሉ አዳዲስ ነገሮች ጨምሮ የታቀደውን ፕሮግራም መሰረታዊ ነገሮች
ያቀርባል፤ የመንገድ መታጠፊያ ጠርዝ ስራ አስኪያጅ የደንበኛ አገልግሎት ስልጠና ላይ ማተኮር እና ተገዢነትን ማስፈጸም፤ እና
የአሽከርካሪ ስልጠና እና እድገት ፕሮግራሞች ላይ ጥናት ማድረግ።
የትዕዛዙ ጽሁፍ
የወደብ ኮሚቴው በሲያትል-ታኮማ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት
ክፍያ ፕሮግራም የሚከተሉትን መሰረታዊ ነገሮች እንዲያካትት ዋና ዳይሬክተሩን ያዛል።
• ወደቡ ከአሁኑ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ለሙከራ የተሰራ ፕሮግራም ጋር
በመተባበር የታክሲ ፈቃድ ካላቸው ባለቤቶች ጋር ወደ አዲስ የስራ ስምምነቶች ይገባል፤ የታክሲ ፈቃድ ያላቸው ባለቤቶች
እስከ ማርች 1፣ 2028 ድረስ ይቆያሉ።
• በአቪዬሽን ሰራተኞች እንደዚህ አይነት አላማዎች እንዴት እንደሚገለጹ ለአሽከርካሪዎች መመሪያ ለመስጠት፣ የስራ
ስምምነቶችን ማስተላለፍ ህጋዊ ለሆኑ አላማዎች ብቻ የሚፈቀድ ይሆናል።
• ወደቡ ከሾፌሩ እስከ SEA በቀጥታ ከሚከፍለው ሁሉን ያካተተ፣ $6/ጉዞ የጉዞ ክፍያ የሚወስድ ይሆናል።
• በየትኛውም የቨርቿል ወረፋ አማራጭ ትግበራ የኮሚቴ እርምጃ እንደሚያስፈልግ በመረዳት፣ ወደቡ ከኦፕሬተሮች ጋር
በመገናኘት፣ በትምህርት፣ እና ከአሽከርካሪው ማህበረሰብ ጋር በመመካከር የቨርቿል ወረፋ አማራጮች ላይ ጥናት
ያደርጋል።
• ወደቡ ከመንገድ ዳር አስተዳደር ጋር ውል እንዲሁም ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል።
• ወደቡ በየሩብ አመቱ ባለ ድርሻ አካላትን ማግኘቱን ይቀጥላል።
• ወደቡ የታክሲ/ የኪራይ ክፍያ ፕሮግራም ላይ የአሽከርካሪዎችን አስተያየት ለማደራጀት በMotion 2019-03
የተፈቀደለትን የበጎ ፈቃደኛ የአሽከርካሪ ድርጅት እውቅና መስጠቱን የሚቀጥል ይሆናል እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኛ
አሽከርካሪዎች ድርጅት ጋር በመደበኛነት መገናኘቱን የሚቀጥል ይሆናል። ወደቡ ፍላጎት ላላቸው አሽከርካሪዎች
የአሽከርካሪ ስልጠና እና የሰው ሃይል እድገት ፕሮግራም ላይ ጥናት ማድረግ እና ማዘጋጀት አለበት።
የአጀንዳ ተራ ቁጥር 10c_ትዕዛዝ የስብሰባ
ቀን፦ ፌብሩዋሪ 14፣ 2023